የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ቆሮንቶስ 16
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ቆሮንቶስ የመጽሐፉ ይዘት

      • በኢየሩሳሌም ላሉ ክርስቲያኖች መዋጮ ማሰባሰብ (1-4)

      • የጳውሎስ የጉዞ ዕቅድ (5-9)

      • ጢሞቴዎስና አጵሎስ ወደ ቆሮንቶስ ሊመጡ እንደሚችሉ ተነገረ (10-12)

      • ማሳሰቢያዎችና ሰላምታዎች (13-24)

1 ቆሮንቶስ 16:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 24:17፤ ሮም 15:26፤ 2ቆሮ 8:3, 4

1 ቆሮንቶስ 16:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 8:19

1 ቆሮንቶስ 16:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 19:21፤ 2ቆሮ 1:15, 16

1 ቆሮንቶስ 16:7

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 20:2

1 ቆሮንቶስ 16:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 19:1

1 ቆሮንቶስ 16:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 19:10, 11

1 ቆሮንቶስ 16:10

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 16:1, 2
  • +ፊልጵ 2:19, 20

1 ቆሮንቶስ 16:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 18:24, 25

1 ቆሮንቶስ 16:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ደፋሮች ሁኑ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ተሰ 5:6
  • +1ቆሮ 15:58፤ ፊልጵ 1:27
  • +ሥራ 4:29
  • +ኤፌ 6:10፤ ቆላ 1:11

1 ቆሮንቶስ 16:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 13:4፤ 1ጴጥ 4:8

1 ቆሮንቶስ 16:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “የአካይያ በኩራት።”

1 ቆሮንቶስ 16:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ፊልጵ 2:29, 30፤ 1ተሰ 5:12፤ 1ጢሞ 5:17

1 ቆሮንቶስ 16:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 1:16

1 ቆሮንቶስ 16:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 16:3, 5፤ ፊል 2

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ቆሮ. 16:1ሥራ 24:17፤ ሮም 15:26፤ 2ቆሮ 8:3, 4
1 ቆሮ. 16:32ቆሮ 8:19
1 ቆሮ. 16:5ሥራ 19:21፤ 2ቆሮ 1:15, 16
1 ቆሮ. 16:7ሥራ 20:2
1 ቆሮ. 16:8ሥራ 19:1
1 ቆሮ. 16:9ሥራ 19:10, 11
1 ቆሮ. 16:10ሥራ 16:1, 2
1 ቆሮ. 16:10ፊልጵ 2:19, 20
1 ቆሮ. 16:12ሥራ 18:24, 25
1 ቆሮ. 16:131ተሰ 5:6
1 ቆሮ. 16:131ቆሮ 15:58፤ ፊልጵ 1:27
1 ቆሮ. 16:13ሥራ 4:29
1 ቆሮ. 16:13ኤፌ 6:10፤ ቆላ 1:11
1 ቆሮ. 16:141ቆሮ 13:4፤ 1ጴጥ 4:8
1 ቆሮ. 16:16ፊልጵ 2:29, 30፤ 1ተሰ 5:12፤ 1ጢሞ 5:17
1 ቆሮ. 16:171ቆሮ 1:16
1 ቆሮ. 16:19ሮም 16:3, 5፤ ፊል 2
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ቆሮንቶስ 16:1-24

ለቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈ የመጀመሪያው ደብዳቤ

16 ለቅዱሳን መዋጮ ማሰባሰብን በተመለከተ+ ደግሞ በገላትያ ለሚገኙ ጉባኤዎች የሰጠሁትን መመሪያ መከተል ትችላላችሁ። 2 መዋጮ የሚሰባሰበው እኔ በምመጣበት ጊዜ እንዳይሆን ከእናንተ እያንዳንዱ በየሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን አቅሙ በሚፈቅድለት መጠን የተወሰነ ገንዘብ ያስቀምጥ። 3 ስመጣም የመረጣችኋቸውንና የድጋፍ ደብዳቤ የጻፋችሁላቸውን ሰዎች+ የልግስና ስጦታችሁን ኢየሩሳሌም እንዲያደርሱ እልካቸዋለሁ። 4 ይሁን እንጂ የእኔም መሄድ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ አብረውኝ ይሄዳሉ።

5 ይሁንና በመቄዶንያ በኩል ማለፌ ስለማይቀር በዚያ ሳልፍ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤+ 6 ወደምሄድበትም ቦታ የተወሰነ መንገድ እንድትሸኙኝ ምናልባት እናንተ ጋ ልቆይ እችላለሁ፤ እንዲያውም ክረምቱን ከእናንተ ጋር አሳልፍ ይሆናል። 7 ይሖዋ* ቢፈቅድ ከእናንተ ጋር የተወሰነ ጊዜ አሳልፋለሁ ብዬ ተስፋ ስለማደርግ አሁን እግረ መንገዴን ሳልፍ ላያችሁ አልፈልግም።+ 8 ይሁንና እስከ ጴንጤቆስጤ በዓል ድረስ በኤፌሶን+ እቆያለሁ፤ 9 ምክንያቱም ትልቅ የሥራ በር ተከፍቶልኛል፤+ ሆኖም ብዙ ተቃዋሚዎች አሉ።

10 ጢሞቴዎስ+ ከመጣ በመካከላችሁ በሚቆይበት ጊዜ ፍርሃት እንዳይሰማው ተባበሩት፤ እሱም እንደ እኔ የይሖዋን* ሥራ የሚሠራ ነውና።+ 11 ስለዚህ ማንም አይናቀው። ከወንድሞች ጋር እየጠበቅኩት ስለሆነ ወደ እኔ እንዲመጣ በሰላም ሸኙት።

12 ወንድማችንን አጵሎስን+ በተመለከተ ደግሞ ከወንድሞች ጋር ወደ እናንተ እንዲመጣ አጥብቄ ለምኜው ነበር። እሱ አሁን የመምጣት ሐሳብ የለውም፤ ሆኖም ሁኔታው ሲመቻችለት ይመጣል።

13 ነቅታችሁ ኑሩ፤+ በእምነት ጸንታችሁ ቁሙ፤+ ወንድ ሁኑ፤*+ ብርቱዎች ሁኑ።+ 14 የምታደርጉትን ነገር ሁሉ በፍቅር አድርጉ።+

15 እንግዲህ ወንድሞች ይህን አሳስባችኋለሁ፦ የእስጢፋናስ ቤተሰብ በአካይያ የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት* እንደሆኑና ቅዱሳንን ለማገልገል ራሳቸውን እንደሰጡ ታውቃላችሁ። 16 እናንተም እንደ እነሱ ላሉት እንዲሁም ከእኛ ጋር ለሚተባበሩትና በትጋት ለሚሠሩት ሁሉ ተገዙ።+ 17 እስጢፋናስ+ እና ፈርጡናጦስ እንዲሁም አካይቆስ እዚህ በመገኘታቸው እጅግ ተደስቻለሁ፤ ምክንያቱም የእናንተ እዚህ አለመኖር በእነሱ ተካክሷል። 18 እነሱ የእኔንም ሆነ የእናንተን መንፈስ አድሰዋልና። ስለዚህ እንዲህ ላሉት ሰዎች እውቅና ስጡ።

19 በእስያ ያሉ ጉባኤዎች ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ እንዲሁም በቤታቸው ያለው ጉባኤ+ ሞቅ ያለ ክርስቲያናዊ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። 20 ወንድሞች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። እርስ በርሳችሁ በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተለዋወጡ።

21 እኔ ጳውሎስ በገዛ እጄ የጻፍኩላችሁ ሰላምታ ይድረሳችሁ።

22 ጌታን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታችን ሆይ፣ ና! 23 የጌታ ኢየሱስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን። 24 የክርስቶስ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የሆናችሁ ሁሉ፣ ፍቅሬ ይድረሳችሁ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ