የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መሳፍንት 18
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

መሳፍንት የመጽሐፉ ይዘት

      • ዳናውያን ተጨማሪ ርስት ፈለጉ (1-31)

        • ዳናውያን የሚክያስን ጣዖታትና ካህን ወሰዱ (14-20)

        • ላይሽን ያዟት፤ ዳን ብለው ጠሯት (27-29)

        • ዳን ውስጥ የጣዖት አምልኮ ተስፋፋ (30, 31)

መሳፍንት 18:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 8:23፤ 1ሳሙ 8:4, 5
  • +ኢያሱ 19:40
  • +ኢያሱ 19:47, 48፤ መሳ 1:34

መሳፍንት 18:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 19:41, 48
  • +መሳ 17:1, 5

መሳፍንት 18:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አነጋገር።”

መሳፍንት 18:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 17:9, 10

መሳፍንት 18:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 19:47, 48፤ መሳ 18:29
  • +መሳ 18:27

መሳፍንት 18:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 15:20, 33፤ መሳ 18:2

መሳፍንት 18:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 18:7, 27
  • +ዘፀ 3:8፤ ዘዳ 8:7-9

መሳፍንት 18:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 18:2

መሳፍንት 18:12

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “የዳን ሰፈር” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 7:1
  • +መሳ 13:24, 25

መሳፍንት 18:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 17:1, 5

መሳፍንት 18:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የቤት ውስጥ አማልክት፤ ጣዖታት።”

  • *

    ወይም “ቀልጦ የተሠራ ሐውልት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 18:2, 29
  • +ዘዳ 27:15፤ መሳ 17:4, 5

መሳፍንት 18:15

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 17:7, 12፤ 18:30

መሳፍንት 18:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 18:11

መሳፍንት 18:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የቤት ውስጥ አማልክቱንና፤ ጣዖታቱንና።”

  • *

    ወይም “ቀልጦ የተሠራውን ሐውልት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 18:2
  • +ዘፀ 28:6፤ መሳ 8:27
  • +ዘፍ 31:19
  • +ዘሌ 19:4፤ ዘዳ 27:15፤ መሳ 17:3-5
  • +መሳ 17:12

መሳፍንት 18:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የቤት ውስጥ አማልክቱንና፤ ጣዖታቱንና።”

  • *

    ወይም “ቀልጦ የተሠራውን ሐውልት።”

መሳፍንት 18:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አማካሪና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 17:12
  • +መሳ 18:30

መሳፍንት 18:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የቤት ውስጥ አማልክቱንና፤ ጣዖታቱንና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 17:4, 5

መሳፍንት 18:25

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በነፍሳቸው የተመረሩ ሰዎች።”

  • *

    ወይም “ነፍስህንና።”

  • *

    ወይም “ነፍስ።”

መሳፍንት 18:27

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 19:47, 48፤ መሳ 18:29
  • +መሳ 18:7, 10

መሳፍንት 18:28

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 13:17, 21

መሳፍንት 18:29

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 30:6፤ 32:28
  • +ኢያሱ 19:47, 48፤ መሳ 20:1፤ 1ነገ 4:25፤ 12:28, 29
  • +መሳ 18:7

መሳፍንት 18:30

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መሳ 17:1, 4፤ 18:18
  • +ዘፀ 2:21, 22
  • +መሳ 17:12

መሳፍንት 18:31

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 40:2፤ ኢያሱ 18:1፤ 1ሳሙ 1:3

ተዛማጅ ሐሳብ

መሳ. 18:1መሳ 8:23፤ 1ሳሙ 8:4, 5
መሳ. 18:1ኢያሱ 19:40
መሳ. 18:1ኢያሱ 19:47, 48፤ መሳ 1:34
መሳ. 18:2ኢያሱ 19:41, 48
መሳ. 18:2መሳ 17:1, 5
መሳ. 18:4መሳ 17:9, 10
መሳ. 18:7ኢያሱ 19:47, 48፤ መሳ 18:29
መሳ. 18:7መሳ 18:27
መሳ. 18:8ኢያሱ 15:20, 33፤ መሳ 18:2
መሳ. 18:10መሳ 18:7, 27
መሳ. 18:10ዘፀ 3:8፤ ዘዳ 8:7-9
መሳ. 18:11መሳ 18:2
መሳ. 18:121ሳሙ 7:1
መሳ. 18:12መሳ 13:24, 25
መሳ. 18:13መሳ 17:1, 5
መሳ. 18:14መሳ 18:2, 29
መሳ. 18:14ዘዳ 27:15፤ መሳ 17:4, 5
መሳ. 18:15መሳ 17:7, 12፤ 18:30
መሳ. 18:16መሳ 18:11
መሳ. 18:17መሳ 18:2
መሳ. 18:17ዘፀ 28:6፤ መሳ 8:27
መሳ. 18:17ዘፍ 31:19
መሳ. 18:17ዘሌ 19:4፤ ዘዳ 27:15፤ መሳ 17:3-5
መሳ. 18:17መሳ 17:12
መሳ. 18:19መሳ 17:12
መሳ. 18:19መሳ 18:30
መሳ. 18:20መሳ 17:4, 5
መሳ. 18:27ኢያሱ 19:47, 48፤ መሳ 18:29
መሳ. 18:27መሳ 18:7, 10
መሳ. 18:28ዘኁ 13:17, 21
መሳ. 18:29ዘፍ 30:6፤ 32:28
መሳ. 18:29ኢያሱ 19:47, 48፤ መሳ 20:1፤ 1ነገ 4:25፤ 12:28, 29
መሳ. 18:29መሳ 18:7
መሳ. 18:30መሳ 17:1, 4፤ 18:18
መሳ. 18:30ዘፀ 2:21, 22
መሳ. 18:30መሳ 17:12
መሳ. 18:31ዘፀ 40:2፤ ኢያሱ 18:1፤ 1ሳሙ 1:3
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
  • 27
  • 28
  • 29
  • 30
  • 31
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
መሳፍንት 18:1-31

መሳፍንት

18 በዚያ ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም።+ በዚያ ጊዜ የዳናውያን ነገድ+ የሚሰፍርበት ርስት እየፈለገ ነበር፤ ምክንያቱም ዳናውያን እስከዚያ ጊዜ ድረስ በእስራኤል ነገዶች መካከል ርስት አልተሰጣቸውም ነበር።+

2 ዳናውያን ከቤተሰባቸው መካከል ብቃት ያላቸውን አምስት ወንዶች መርጠው ምድሪቱን እንዲሰልሉና እንዲቃኙ ከጾራና ከኤሽታዖል+ ላኳቸው። እነሱንም “ሂዱ፣ ምድሪቱን ቃኙ” አሏቸው። እነሱም በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ ወደሚገኘው ወደ ሚክያስ+ ቤት ሲደርሱ እዚያ አደሩ። 3 ወደ ሚክያስ ቤት በቀረቡም ጊዜ የወጣቱን ሌዋዊ ድምፅ* ለዩት፤ በመሆኑም ወደ እሱ ገብተው “ለመሆኑ እዚህ ማን አመጣህ? ደግሞስ እዚህ ምን ትሠራለህ? እዚህ እንድትቆይ ያደረገህስ ምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት። 4 እሱም መልሶ “ሚክያስ ይህን ይህን አደረገልኝ፤ ካህን ሆኜ እንዳገለግለውም ቀጠረኝ”+ አላቸው። 5 ከዚያም እነሱ “መንገዳችን የተቃና መሆን አለመሆኑን እባክህ አምላክን ጠይቅልን” አሉት። 6 ካህኑም “በሰላም ሂዱ። በመንገዳችሁ ሁሉ ይሖዋ ከእናንተ ጋር ነው” አላቸው።

7 ስለሆነም አምስቱ ሰዎች ጉዟቸውን በመቀጠል ወደ ላይሽ+ መጡ። የከተማዋም ሰዎች ልክ እንደ ሲዶናውያን ራሳቸውን ችለው እንደሚኖሩ ተመለከቱ። እነዚህ ሰዎች ያለምንም ስጋት ተረጋግተው የተቀመጡ+ ከመሆናቸውም ሌላ በምድሪቱ ላይ እነሱን የሚያውክ ጨቋኝ ቅኝ ገዢ አልነበረም። በተጨማሪም የሚኖሩት ከሲዶናውያን ርቀው ነበር፤ ከማንም ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት አልነበራቸውም።

8 እነሱም በጾራና በኤሽታዖል+ ወደሚገኙት ወንድሞቻቸው በተመለሱ ጊዜ ወንድሞቻቸው “የሄዳችሁበት ጉዳይ እንዴት ሆነ?” በማለት ጠየቋቸው። 9 እነሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ “ምድሪቱ በጣም ጥሩ ምድር መሆኗን ስላየን ተነሱ፣ እንዝመትባቸው። ለምን ታመነታላችሁ? ገብታችሁ ምድሪቱን ለመውረስ አትዘግዩ። 10 እዚያ ስትደርሱ ያለምንም ስጋት የተቀመጠ+ ሕዝብ ታገኛላችሁ፤ ምድሪቱም በጣም ሰፊ ነች። አምላክም በምድር ላይ ያለ ማንኛውም ነገር የማይታጣበትን ስፍራ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቷችኋል።”+

11 ከዚያም ከዳናውያን ቤተሰብ የሆኑና ለጦርነት የታጠቁ 600 ሰዎች ከጾራና ከኤሽታዖል+ ተንቀሳቀሱ። 12 እነሱም ወጥተው በይሁዳ በምትገኘው በቂርያትየአሪም+ ሰፈሩ። ከቂርያትየአሪም በስተ ምዕራብ የሚገኘው ያ ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ ማሃነህዳን* + ተብሎ የሚጠራው በዚህ የተነሳ ነው። 13 ከዚያም ተነስተው ወደ ኤፍሬም ተራራማ አካባቢ ተጓዙ፤ ወደ ሚክያስም+ ቤት መጡ።

14 በኋላም ላይሽን+ ለመሰለል ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎች ወንድሞቻቸውን “እነዚህ ቤቶች ውስጥ ኤፉድ፣ የተራፊም ቅርጻ ቅርጾች፣* የተቀረጸ ምስልና ከብረት የተሠራ ሐውልት* እንዳለ ታውቃላችሁ?+ እንግዲህ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ አስቡ” አሏቸው። 15 እነሱም በሚክያስ ቤት ወደሚገኘው ወደ ወጣቱ ሌዋዊ+ ቤት ጎራ ብለው ስለ ደህንነቱ ጠየቁት። 16 በዚህ ጊዜ ሁሉ ለጦርነት የታጠቁት 600ዎቹ የዳን ሰዎች+ መግቢያው በር ላይ ቆመው ነበር። 17 ምድሪቱን ለመሰለል+ ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎችም የተቀረጸውን ምስል፣ ኤፉዱን፣+ የተራፊም ቅርጻ ቅርጾቹንና* + ከብረት የተሠራውን ምስል* + ለመውሰድ ወደ ውስጥ ገቡ። (ካህኑም+ ለጦርነት ከታጠቁት 600 ሰዎች ጋር መግቢያው በር ላይ ቆሞ ነበር።) 18 እነሱም ወደ ሚክያስ ቤት ገብተው የተቀረጸውን ምስል፣ ኤፉዱን፣ የተራፊም ቅርጻ ቅርጾቹንና* ከብረት የተሠራውን ምስል* ወሰዱ። ካህኑም “ምን እያደረጋችሁ ነው?” አላቸው። 19 እነሱ ግን እንዲህ አሉት፦ “ዝም በል። ምንም ቃል አትናገር፤ ይልቅስ ከእኛ ጋር ሄደህ አባትና* ካህን ሁነን። ለአንድ ሰው ቤት ካህን ብትሆን ይሻልሃል+ ወይስ በእስራኤል ለሚገኝ አንድ ነገድና+ ቤተሰብ ካህን ብትሆን?” 20 በዚህ ጊዜ የካህኑ ልብ ደስ ተሰኘ፤ እሱም ኤፉዱን፣ የተራፊም ቅርጻ ቅርጾቹንና* የተቀረጸውን ምስል+ ይዞ ከሕዝቡ ጋር ሄደ።

21 ከዚያም ልጆቹን፣ ከብቶቹንና ውድ የሆኑትን ነገሮች ከፊት አስቀድመው ጉዟቸውን ለመቀጠል ተነሱ። 22 ከሚክያስ ቤት የተወሰነ መንገድ ርቀው ከሄዱም በኋላ በሚክያስ ቤት አቅራቢያ በሚገኙ ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች አንድ ላይ ተሰበሰቡ፤ ዳናውያንንም ተከታትለው ደረሱባቸው። 23 ከዚያም ጮኸው ሲጠሯቸው ዳናውያኑ ዞር በማለት ሚክያስን “ምን ሆነሃል? ተሰባስባችሁ የመጣችሁትስ ለምንድን ነው?” አሉት። 24 እሱም “የሠራኋቸውን አማልክቴን ወሰዳችሁ፤ ካህኑንም ይዛችሁ ሄዳችሁ። እንግዲህ ምን ቀረኝ? ታዲያ እንዴት ‘ምን ሆነሃል?’ ትሉኛላችሁ?” አላቸው። 25 በዚህ ጊዜ ዳናውያኑ “አትጩኽብን፤ አለዚያ የተቆጡ ሰዎች* ጉዳት ያደርሱባችኋል፤ ይህም የገዛ ሕይወትህንና* የቤተሰብህን ሕይወት* ሊያሳጣህ ይችላል” አሉት። 26 ዳናውያኑም ጉዟቸውን ቀጠሉ፤ ሚክያስም እነሱ ከእሱ ይልቅ ብርቱዎች እንደሆኑ ስለተረዳ ተመልሶ ወደ ቤቱ ሄደ።

27 እነሱም ሚክያስ የሠራቸውን ነገሮችና የእሱን ካህን ከወሰዱ በኋላ ወደ ላይሽ+ ይኸውም ያለምንም ስጋት ተረጋግተው ይኖሩ ወደነበሩት+ ሰዎች ሄዱ። እነሱንም በሰይፍ መቷቸው፤ ከተማዋንም በእሳት አቃጠሉ። 28 ከተማዋ የምትገኘው ከሲዶና ርቃ ስለነበርና ነዋሪዎቿም ከማንኛውም ሕዝብ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ስላልነበራቸው ማንም የሚያድናት አልነበረም፤ ላይሽ የምትገኘው በቤትሬሆብ+ ባለው ሸለቋማ ሜዳ* ላይ ነበር። እነሱም ከተማዋን ዳግመኛ ገንብተው በዚያ መኖር ጀመሩ። 29 በተጨማሪም ከተማዋን ለእስራኤል በተወለደለት+ በአባታቸው በዳን ስም ዳን+ ብለው ጠሯት። የከተማዋ የቀድሞ ስም ግን ላይሽ ነበር።+ 30 ከዚያም ዳናውያን የተቀረጸውን ምስል+ ለራሳቸው አቆሙት፤ የሙሴ ልጅ የሆነው የጌርሳም+ ልጅ ዮናታንና+ ወንዶች ልጆቹ የምድሪቱ ነዋሪዎች በግዞት እስከተወሰዱበት ጊዜ ድረስ የዳናውያን ነገድ ካህናት ሆኑ። 31 ሚክያስ የሠራውንም የተቀረጸ ምስል አቆሙት፤ ምስሉም የእውነተኛው አምላክ ቤት በሴሎ በነበረበት ጊዜ ሁሉ በዚያ ነበር።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ