-
1 ዜና መዋዕል 1:43-50አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
43 እነዚህ በእስራኤላውያን*+ ላይ የትኛውም ንጉሥ መግዛት ከመጀመሩ በፊት በኤዶም+ ምድር ይገዙ የነበሩ ነገሥታት ናቸው፦ የቢዖር ልጅ ቤላ፣ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር። 44 ቤላ ሲሞት የቦስራው+ የዛራ ልጅ ዮባብ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 45 ዮባብ ሲሞት ከቴማናውያን ምድር የመጣው ሁሻም በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 46 ሁሻም ሲሞት ምድያምን በሞዓብ ምድር* ድል ያደረገው የቤዳድ ልጅ ሃዳድ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። የከተማው ስም አዊት ይባል ነበር። 47 ሃዳድ ሲሞት የማስረቃው ሳምላ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 48 ሳምላ ሲሞት በወንዙ አጠገብ ያለው የረሆቦቱ ሻኡል በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 49 ሻኡል ሲሞት የአክቦር ልጅ ባአልሀናን በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 50 ባአልሀናን ሲሞት ሃዳድ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። የከተማውም ስም ጳኡ ነበር፤ የሚስቱም ስም መሄጣቤል ሲሆን እሷም የመዛሃብ ሴት ልጅ የማጥሬድ ልጅ ናት።
-