-
ዘፀአት 31:2-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 “እንግዲህ እኔ ከይሁዳ ነገድ የሆነው የሁር ልጅ ዖሪ+ የወለደውን ባስልኤልን+ መርጬዋለሁ።* 3 ደግሞም ጥበብ፣ ማስተዋልና እውቀት በመስጠት በማንኛውም ዓይነት የእጅ ሙያ የተካነ እንዲሆን በአምላክ መንፈስ እሞላዋለሁ፤ 4 ይህን የማደርገው የተለያዩ ንድፎችን እንዲያወጣ፣ በወርቅ፣ በብርና በመዳብ የተለያዩ ነገሮችን እንዲሠራ፣ 5 ፈርጥ የሚሆኑትን ድንጋዮች እንዲቀርጽና በቦታቸው እንዲያስቀምጥ+ እንዲሁም ከእንጨት ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን እንዲሠራ ነው።+ 6 በተጨማሪም ከዳን ነገድ የሆነውን የአሂሳማክን ልጅ ኤልያብን+ ረዳት እንዲሆነው መርጬዋለሁ፤ እኔ ያዘዝኩህን የሚከተሉትን ነገሮች በሙሉ እንዲሠሩ ጥሩ ችሎታ* ባላቸው ሰዎች ሁሉ ልብ ውስጥ ጥበብን አኖራለሁ፦+
-