19 “ከ20ዎቹ ቋሚዎች ሥር የሚሆኑ 40 የብር መሰኪያዎችን+ ትሠራለህ፤ በአንዱ ቋሚ ሥር ያሉት ሁለት ጉጦች ሁለት መሰኪያዎች፣ ቀጥሎ ባለው በእያንዳንዱ ቋሚ ሥር ያሉት ሁለት ጉጦችም+ ሁለት መሰኪያዎች ይኖሯቸዋል። 20 በስተ ሰሜን በኩል ላለው ለሌላኛውም የማደሪያ ድንኳኑ ጎን 20 ቋሚዎችን ሥራ፤ 21 እንዲሁም 40 የብር መሰኪያዎቻቸውን ሥራ፤ በአንዱ ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያዎች፣ ቀጥሎ ባለው በእያንዳንዱም ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያዎች ይኑሩ።