-
ዘፀአት 36:24-26አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 ከዚያም በ20ዎቹ ቋሚዎች ሥር የሚሆኑ 40 የብር መሰኪያዎችን ሠራ፤ በአንዱ ቋሚ ሥር ላሉት ሁለት ጉጦች የሚሆኑ ሁለት መሰኪያዎችን፣ ቀጥሎ ባለው በእያንዳንዱም ቋሚ ሥር ላሉት ሁለት ጉጦች የሚሆኑ ሁለት መሰኪያዎችን አደረገ።+ 25 በስተ ሰሜን በኩል ላለው ለሌላኛውም የማደሪያ ድንኳኑ ጎን 20 ቋሚዎችን ሠራ፤ 26 እንዲሁም 40 የብር መሰኪያዎቻቸውን ሠራ፤ በአንዱ ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያዎችን፣ በተቀረው በእያንዳንዱም ቋሚ ሥር ሁለት መሰኪያዎችን አደረገ።
-