-
ዘፀአት 25:10-15አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 “ርዝመቱ ሁለት ክንድ* ተኩል፣ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል እንዲሁም ከፍታው አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ታቦት* ከግራር እንጨት ይሠራሉ።+ 11 ከዚያም በንጹሕ ወርቅ ትለብጠዋለህ።+ ውስጡንና ውጭውን ትለብጠዋለህ፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ ትሠራለታለህ።+ 12 አራት የወርቅ ቀለበቶች ትሠራለታለህ፤ ከዚያም ሁለቱን ቀለበቶች በአንዱ በኩል ሁለቱን ቀለበቶች ደግሞ በሌላው በኩል በማድረግ ከአራቱ እግሮቹ በላይ ታያይዛቸዋለህ። 13 ከግራር እንጨት መሎጊያዎችን ትሠራለህ፤ በወርቅም ትለብጣቸዋለህ።+ 14 ታቦቱን ለመሸከም እንዲያገለግሉ መሎጊያዎቹን በታቦቱ ጎንና ጎን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ ታስገባቸዋለህ። 15 መሎጊያዎቹ በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ እንዳሉ ይቀመጣሉ፤ ከዚያ መውጣት የለባቸውም።+
-