ዘፀአት 30:34, 35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንተም ጥሩ መዓዛ ካላቸው ቅመሞች+ ይኸውም ከሚንጠባጠብ ሙጫ፣ ከኦኒካ፣* ከሚሸት ሙጫ እንዲሁም ከንጹሕ ነጭ ዕጣን እኩል መጠን ውሰድ። 35 ከዚያም ዕጣን አድርገህ አዘጋጀው፤+ ይህም ዕጣን በብልሃት የተቀመመ፣ ጨው የተጨመረበት፣+ ንጹሕና ቅዱስ መሆን ይኖርበታል። መዝሙር 141:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ጸሎቴ በአንተ ፊት እንደተዘጋጀ ዕጣን ይሁን፤+የተዘረጉት እጆቼ ምሽት ላይ እንደሚቀርብ የእህል መባ ይሁኑ።+
34 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንተም ጥሩ መዓዛ ካላቸው ቅመሞች+ ይኸውም ከሚንጠባጠብ ሙጫ፣ ከኦኒካ፣* ከሚሸት ሙጫ እንዲሁም ከንጹሕ ነጭ ዕጣን እኩል መጠን ውሰድ። 35 ከዚያም ዕጣን አድርገህ አዘጋጀው፤+ ይህም ዕጣን በብልሃት የተቀመመ፣ ጨው የተጨመረበት፣+ ንጹሕና ቅዱስ መሆን ይኖርበታል።