-
ዘፀአት 7:5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 በግብፅ ላይ እጄን ስዘረጋና እስራኤላውያንን ከመካከላቸው ሳወጣ ግብፃውያን እኔ ይሖዋ መሆኔን በእርግጥ ያውቃሉ።”+
-
-
ዘፀአት 9:15, 16አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 እስካሁን እጄን ዘርግቼ አንተንም ሆነ ሕዝብህን አጥፊ በሆነ መቅሰፍት በመታኋችሁ ነበር፤ አንተም ከምድር ገጽ ተጠራርገህ በጠፋህ ነበር። 16 ሆኖም ኃይሌን እንዳሳይህና ስሜ በመላው ምድር እንዲታወጅ ስል በሕይወት አቆይቼሃለሁ።+
-
-
2 ነገሥት 18:28አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
28 ከዚያም ራብሻቁ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ በአይሁዳውያን ቋንቋ እንዲህ አለ፦ “የታላቁን ንጉሥ፣ የአሦርን ንጉሥ ቃል ስሙ።+
-
-
2 ነገሥት 18:35አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
35 ከእነዚህ አገሮች አማልክት ሁሉ ምድሩን ከእጄ ማስጣል የቻለ የትኛው ነው? ታዲያ ይሖዋ ኢየሩሳሌምን ከእጄ ሊያስጥላት ይችላል?”’”+
-