-
ዘፀአት 7:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 ሙሴና አሮን ወዲያውኑ ልክ ይሖዋ እንዳዘዛቸው አደረጉ። እሱም ፈርዖንና አገልጋዮቹ እያዩ በትሩን አንስቶ በአባይ ወንዝ ውስጥ ያለውን ውኃ መታ፤ በወንዙ ውስጥ የነበረውም ውኃ በሙሉ ወደ ደም ተለወጠ።+
-
-
ዘፀአት 9:11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 አስማተኞቹ ካህናት በእባጩ የተነሳ ሙሴ ፊት ሊቆሙ አልቻሉም፤ ምክንያቱም እባጩ በአስማተኞቹ ካህናትና በሁሉም ግብፃውያን ላይ ወጥቶ ነበር።+
-
-
2 ጢሞቴዎስ 3:8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 እንግዲህ ኢያኔስና ኢያንበሬስ ሙሴን እንደተቃወሙት ሁሉ እነዚህም እውነትን ይቃወማሉ። እንዲህ ያሉ ሰዎች አእምሯቸው ሙሉ በሙሉ የተበላሸ ከመሆኑም ሌላ በእምነት ጎዳና ስለማይመላለሱ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት አጥተዋል።
-