-
ዘፀአት 7:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 ሙሴና አሮን ወዲያውኑ ልክ ይሖዋ እንዳዘዛቸው አደረጉ። እሱም ፈርዖንና አገልጋዮቹ እያዩ በትሩን አንስቶ በአባይ ወንዝ ውስጥ ያለውን ውኃ መታ፤ በወንዙ ውስጥ የነበረውም ውኃ በሙሉ ወደ ደም ተለወጠ።+
-
-
ዘፀአት 8:7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 ይሁን እንጂ አስማተኞቹ ካህናትም በሚስጥራዊ ጥበባቸው ተመሳሳይ ነገር ፈጸሙ፤ እነሱም እንቁራሪቶች በግብፅ ምድር ላይ እንዲወጡ አደረጉ።+
-
-
ዘፀአት 8:18አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 አስማተኞቹ ካህናትም ተመሳሳይ ነገር ለመፈጸምና በሚስጥራዊ ጥበባቸው ትንኞች እንዲፈሉ ለማድረግ ሞከሩ፤+ ሆኖም አልቻሉም። ትንኞቹ ሰዉንም እንስሳውንም ወርረው ነበር።
-
-
2 ጢሞቴዎስ 3:8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 እንግዲህ ኢያኔስና ኢያንበሬስ ሙሴን እንደተቃወሙት ሁሉ እነዚህም እውነትን ይቃወማሉ። እንዲህ ያሉ ሰዎች አእምሯቸው ሙሉ በሙሉ የተበላሸ ከመሆኑም ሌላ በእምነት ጎዳና ስለማይመላለሱ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት አጥተዋል።
-