የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 22:29
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 29 “ከተትረፈረፈው ምርትህና ሞልቶ ከሚፈሰው መጭመቂያህ* መባ ለማቅረብ አትሳሳ።+ የወንዶች ልጆችህን በኩር ለእኔ መስጠት አለብህ።+

  • ዘፀአት 34:19, 20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 “በኩር የሆነ ወንድ ሁሉ* የእኔ ነው፤+ ደግሞም የመንጋህ በኩር ሁሉ፣ በኩር የሆነ በሬም ሆነ ተባዕት በግ የእኔ ነው።+ 20 የአህያን በኩር በበግ ዋጀው። የማትዋጀው ከሆነ ግን አንገቱን ስበረው። ከወንዶች ልጆችህ መካከል በኩር የሆነውን ሁሉ ትዋጀዋለህ።+ ማንም ባዶ እጁን ፊቴ አይቅረብ።

  • ዘሌዋውያን 27:26
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 26 “‘ይሁንና ማንም ሰው ከእንስሳት መካከል በኩር የሆነውን ቅዱስ አድርጎ መስጠት የለበትም፤ ምክንያቱም በኩሩ የይሖዋ ነው።+ በሬም ሆነ በግ ቀድሞውንም የይሖዋ ነው።+

  • ዘኁልቁ 3:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ምክንያቱም በኩር ሁሉ የእኔ ነው።+ በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ በመታሁበት ቀን+ በእስራኤላውያን መካከል ያለውን የሰውም ሆነ የእንስሳ በኩር ለራሴ ቀድሻለሁ።+ እነሱ የእኔ ይሆናሉ። እኔ ይሖዋ ነኝ።”

  • ሉቃስ 2:22, 23
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 በተጨማሪም በሙሴ ሕግ መሠረት+ የሚነጹበት ጊዜ ሲደርስ ሕፃኑን በይሖዋ* ፊት ለማቅረብ ወደ ኢየሩሳሌም ይዘውት መጡ፤ 23 ይህን ያደረጉት “በኩር የሆነ ወንድ ሁሉ* ለይሖዋ* የተቀደሰ መሆን አለበት”+ ተብሎ በይሖዋ* ሕግ ላይ በተጻፈው መሠረት ነው።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ