-
ዘፀአት 9:15, 16አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 እስካሁን እጄን ዘርግቼ አንተንም ሆነ ሕዝብህን አጥፊ በሆነ መቅሰፍት በመታኋችሁ ነበር፤ አንተም ከምድር ገጽ ተጠራርገህ በጠፋህ ነበር። 16 ሆኖም ኃይሌን እንዳሳይህና ስሜ በመላው ምድር እንዲታወጅ ስል በሕይወት አቆይቼሃለሁ።+
-
-
ዘፀአት 18:10, 11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 ከዚያም ዮቶር እንዲህ አለ፦ “ከግብፅና ከፈርዖን እጅ ያዳናችሁ እንዲሁም ሕዝቡን ከግብፅ እጅ ነፃ ያወጣው ይሖዋ ይወደስ። 11 ይሖዋ በሕዝቡ ላይ የእብሪት ድርጊት በፈጸሙ ሰዎች ላይ እንዲህ ያለ እርምጃ በመውሰዱ ከሌሎች አማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ+ አሁን አውቄአለሁ።”
-