የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 10:15-17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ከነአን የበኩር ልጁን ሲዶናን፣+ ሄትን+ 16 እንዲሁም ኢያቡሳዊውን፣+ አሞራዊውን፣+ ገርጌሻዊውን፣ 17 ሂዋዊውን፣+ አርቃዊውን፣ ሲናዊውን፣

  • ዘፀአት 33:1, 2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 33 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከግብፅ መርተህ ካወጣኸው ሕዝብ ጋር ከዚህ ተነስተህ ሂድ። ‘ለዘርህ እሰጠዋለሁ’ በማለት ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደማልኩላቸውም ምድር ተጓዝ።+ 2 እኔም ከአንተ አስቀድሜ መልአክ በመላክ+ ከነአናውያንን፣ አሞራውያንን፣ ሂታውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ሂዋውያንንና ኢያቡሳውያንን አስወጣለሁ።+

  • ዘዳግም 7:1
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 “አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርገህ ወደምትወርሳት ምድር ሲያመጣህ+ ብዙ ሕዝብ ያላቸውን ብሔራት ይኸውም ከአንተ ይልቅ ብዙ ሕዝብ ያላቸውንና ኃያላን የሆኑትን ሰባት ብሔራት+ ማለትም ሂታውያንን፣ ገርጌሻውያንን፣ አሞራውያንን፣+ ከነአናውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ሂዋውያንን እና ኢያቡሳውያንን+ ከፊትህ ያስወግድልሃል።+

  • ኢያሱ 3:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 ከዚያም እንዲህ አላቸው፦ “እንግዲህ በመካከላችሁ ሕያው አምላክ እንዳለና+ እሱም ከነአናውያንን፣ ሂታውያንን፣ ሂዋውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ገርጌሻውያንን፣ አሞራውያንንና ኢያቡሳውያንን በእርግጥ ከፊታችሁ እንደሚያባርራቸው በዚህ ታውቃላችሁ።+

  • ነህምያ 9:7, 8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 አብራምን+ መርጠህ ከከለዳውያን ዑር+ ያወጣኸውና አብርሃም+ ብለህ የጠራኸው እውነተኛው አምላክ ይሖዋ አንተ ነህ። 8 ልቡ በፊትህ ታማኝ ሆኖ ስላገኘኸው+ የከነአናውያንን፣ የሂታውያንን፣ የአሞራውያንን፣ የፈሪዛውያንን፣ የኢያቡሳውያንንና የገርጌሻውያንን ምድር ለእሱ ይኸውም ለዘሩ ለመስጠት ከእሱ ጋር ቃል ኪዳን ተጋባህ፤+ ጻድቅ ስለሆንክም ቃልህን ጠበቅክ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ