-
ዘፀአት 24:17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 ሁኔታውን ይከታተሉ ለነበሩት እስራኤላውያን የይሖዋ ክብር በተራራው አናት ላይ እንዳለ የሚባላ እሳት ሆኖ ታያቸው።
-
-
2 ዜና መዋዕል 7:1-3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 ሰለሞንም ጸሎቱን እንደጨረሰ+ እሳት ከሰማያት ወርዶ+ የሚቃጠለውን መባና መሥዋዕቶቹን በላ፤ የይሖዋም ክብር ቤቱን ሞላው።+ 2 የይሖዋ ክብር የይሖዋን ቤት ሞልቶት ስለነበር ካህናቱ ወደ ይሖዋ ቤት መግባት አልቻሉም።+ 3 የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ እሳቱ ሲወርድና የይሖዋ ክብር ከቤቱ በላይ ሲሆን ይመለከቱ ነበር፤ ወደ መሬት አጎንብሰው ድንጋይ በተነጠፈበት ወለል ላይ በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ፤ ደግሞም “እሱ ጥሩ ነውና፤ ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል” እያሉ ይሖዋን አመሰገኑ።
-