-
ዘኁልቁ 35:22-25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 “‘ይሁን እንጂ ሰውየው ግለሰቡን የገፈተረው በጥላቻ ተነሳስቶ ሳይሆን ሳያስበው ከሆነ ወይም ዕቃ የወረወረበት ተንኮል አስቦ* ካልሆነ+ 23 አሊያም ግለሰቡ ሳያየው ድንጋይ ቢጥልበትና ቢሞት ሆኖም ሰውየው ከግለሰቡ ጋር ጠላትነት ባይኖረውና ይህን ያደረገው እሱን ለመጉዳት አስቦ ባይሆን 24 ማኅበረሰቡ እነዚህን ደንቦች መሠረት በማድረግ በገዳዩና በደም ተበቃዩ መካከል ፍርድ ይስጥ።+ 25 ማኅበረሰቡም ነፍሰ ገዳዩን ከደም ተበቃዩ እጅ ታድጎ ሸሽቶበት ወደነበረው የመማጸኛ ከተማ ይመልሰው፤ እሱም በቅዱስ ዘይት የተቀባው+ ሊቀ ካህናት እስኪሞት ድረስ በዚያ ይቆይ።
-
-
ዘዳግም 19:3-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 አምላክህ ይሖዋ እንድትወርሳት የሚሰጥህን ምድር ሦስት ቦታ ከፋፍላት፤ እንዲሁም ነፍስ ያጠፋ ማንኛውም ሰው ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ መሸሽ እንዲችል መንገድ አዘጋጅ።
4 “እዚያ ለመኖር ሸሽቶ የሄደን፣ ነፍስ ያጠፋ ሰው በተመለከተ መደረግ ያለበት ነገር ይህ ነው፦ ለባልንጀራው የቆየ ጥላቻ የሌለው አንድ ሰው ሳያስበው ባልንጀራውን መትቶ ቢገድለው፣+ 5 ለምሳሌ ከባልንጀራው ጋር እንጨት ለመቁረጥ ወደ ጫካ ቢሄድ፣ ዛፉንም ለመቁረጥ መጥረቢያውን በሚሰነዝርበት ጊዜ ብረቱ ከእጀታው ላይ ወልቆ ባልንጀራውን ቢመታውና ቢገድለው ነፍሰ ገዳዩ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ ሕይወቱን ማትረፍ ይችላል።+
-
-
ኢያሱ 20:7-9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 በመሆኑም በንፍታሌም ተራራማ አካባቢ በገሊላ የምትገኘውን ቃዴሽን፣+ በኤፍሬም ተራራማ አካባቢ የምትገኘውን ሴኬምንና+ በይሁዳ ተራራማ አካባቢ የምትገኘውን ቂርያትአርባን+ ማለትም ኬብሮንን ለዚህ ዓላማ ቀደሱ።* 8 ከኢያሪኮ በስተ ምሥራቅ ባለው የዮርዳኖስ ክልል ደግሞ ከሮቤል ነገድ ርስት በአምባው ላይ በሚገኘው ምድረ በዳ ላይ ያለችውን ቤጼርን፣+ ከጋድ ነገድ ርስት በጊልያድ የምትገኘውን ራሞትን+ እንዲሁም ከምናሴ ነገድ ርስት በባሳን የምትገኘውን ጎላንን+ መረጡ።+
9 ሳያስበው ሰው* የገደለ ማንኛውም ግለሰብ በማኅበረሰቡ ፊት ለፍርድ ከመቅረቡ በፊት ደም ተበቃዩ አግኝቶ እንዳይገድለው ሸሽቶ እንዲሸሸግባቸው+ ለእስራኤላውያን በሙሉ ወይም በመካከላቸው ለሚኖር የባዕድ አገር ሰው የተለዩት ከተሞች እነዚህ ናቸው።+
-