-
ዘዳግም 4:15-18አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 “በመሆኑም ይሖዋ በኮሬብ በእሳቱ መካከል ሆኖ ባነጋገራችሁ ቀን ምንም መልክ ስላላያችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፤* 16 ይኸውም ምግባረ ብልሹ በመሆን በማንኛውም ነገር አምሳል የተቀረጸን የትኛውንም ዓይነት ምስል፣ የወንድ ወይም የሴት ምስል፣+ 17 በምድር ላይ ያለን የማንኛውንም እንስሳ ምስል ወይም በሰማይ ላይ የሚበርን የማንኛውንም ወፍ ምስል፣+ 18 መሬት ለመሬት የሚሄድን የማንኛውንም ነገር ምስል አሊያም ከምድር በታች በውኃ ውስጥ ያለን የማንኛውንም ዓሣ ምስል ለራሳችሁ እንዳትሠሩ ነው።+
-