-
ዘፀአት 18:25, 26አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
25 ሙሴም ከመላው እስራኤል ብቃት ያላቸውን ወንዶች መርጦ የሺህ አለቆች፣ የመቶ አለቆች፣ የሃምሳ አለቆችና የአሥር አለቆች አድርጎ በሕዝቡ ላይ ሾማቸው። 26 በመሆኑም እነዚህ ሰዎች የተለያዩ ጉዳዮች በሚነሱበት ጊዜ ሕዝቡን ይዳኙ ነበር። ከበድ ያለ ጉዳይ ሲያጋጥማቸው ወደ ሙሴ ያመጡ+ የነበረ ሲሆን ቀለል ያሉ ጉዳዮችን ግን ራሳቸው ይዳኙ ነበር።
-
-
ዘኁልቁ 27:1-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
27 ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ቤተሰቦች የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የጊልያድ ልጅ፣ የሄፌር ልጅ የሆነው የሰለጰአድ ሴቶች ልጆች+ ቀረቡ። የሴት ልጆቹም ስም ማህላ፣ ኖኅ፣ ሆግላ፣ ሚልካ እና ቲርጻ ነበር። 2 እነሱም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በሙሴ፣ በካህኑ በአልዓዛር፣ በአለቆቹ+ እንዲሁም በመላው ማኅበረሰብ ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፦ 3 “አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ ይሁንና እሱ በይሖዋ ላይ ለማመፅ ከተባበሩት ከቆሬ ግብረ አበሮች+ አንዱ አልነበረም፤ እሱ የሞተው በራሱ ኃጢአት ነው፤ ወንዶች ልጆችም አልነበሩትም። 4 ታዲያ አባታችን ወንድ ልጅ ስለሌለው ብቻ ስሙ ከቤተሰቡ መካከል ለምን ይጥፋ? በአባታችን ወንድሞች መካከል ርስት ስጡን።” 5 ስለዚህ ሙሴ ጉዳያቸውን በይሖዋ ፊት አቀረበ።+
-