-
ዘሌዋውያን 3:9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 ከኅብረት መሥዋዕቱ ላይም ስቡን ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርባል።+ ከጀርባ አጥንቱ አጠገብ ያለውን ላት በሙሉ፣ አንጀቱን የሸፈነውን ስብ፣ በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ በሙሉ ያነሳዋል፤
-
-
ዘሌዋውያን 3:17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 “‘ስብም ሆነ ደም+ ፈጽሞ አትብሉ። ይህም በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለእናንተም ሆነ ለትውልዶቻችሁ ዘላቂ ደንብ ነው።’”
-
-
ዘሌዋውያን 4:8, 9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 “‘ከዚያም አንጀቱን የሸፈነውን ስብና በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ ጨምሮ ለኃጢአት መባ የቀረበውን ወይፈን ስብ በሙሉ ከላዩ ላይ ያነሳል፤ 9 እንዲሁም ሁለቱን ኩላሊቶችና በላያቸው ላይ ያለውን በሽንጡ አካባቢ የሚገኝ ስብ ያነሳል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳል።+
-
-
ዘሌዋውያን 8:18አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 እሱም ለሚቃጠል መባ የሚሆነውን አውራ በግ አመጣ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም እጆቻቸውን በአውራው በግ ራስ ላይ ጫኑ።+
-
-
ዘሌዋውያን 8:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 አውራውንም በግ በየብልቱ ቆራረጠው፤ ቀጥሎም ጭንቅላቱን፣ ብልቶቹንና ሞራውን* አጨሰው።
-