-
ዘኁልቁ 15:2-4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘እንድትኖሩባት ወደምሰጣችሁ ምድር በምትገቡበትና+ 3 ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ+ እንዲሆን የሚቃጠል መባም+ ሆነ ለየት ያለ ስእለት ለመሳል የሚቀርብ መሥዋዕት ወይም የፈቃደኝነት መባ+ አሊያም በየወቅቱ በምታከብሯቸው በዓላት+ ላይ የሚቀርብ መባ፣ ከከብታችሁ ወይም ከመንጋችሁ በመውሰድ ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ በምታቀርቡበት ጊዜ 4 መባውን የሚያቀርበው ሰው በአንድ አራተኛ ሂን* ዘይት የተለወሰ አንድ አሥረኛ ኢፍ* የላመ ዱቄትም+ የእህል መባ አድርጎ ለይሖዋ ማቅረብ ይኖርበታል።
-