-
ዘሌዋውያን 2:3-7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 ከእህል መባው የተረፈው ማንኛውም ነገር የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ነው፤+ ይህም ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች የተረፈ ስለሆነ እጅግ ቅዱስ ነው።+
4 “‘በመጋገሪያ ምድጃ የተጋገረ የእህል መባ የምታቀርብ ከሆነ ከላመ ዱቄት በዘይት ተለውሶ የተጋገረ እርሾ ያልገባበት የቀለበት ቅርጽ ያለው ዳቦ ወይም ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ* መሆን ይኖርበታል።+
5 “‘መባህ በምጣድ የተጋገረ የእህል መባ+ ከሆነ በዘይት ከተለወሰ እርሾ ያልገባበት የላመ ዱቄት የተጋገረ መሆን ይኖርበታል። 6 መቆራረስ አለበት፤ ዘይትም አፍስበት።+ ይህ የእህል መባ ነው።
7 “‘መባህ በድስት የተዘጋጀ የእህል መባ ከሆነ ከላመ ዱቄትና ከዘይት የተሠራ መሆን ይኖርበታል።
-
-
1 ቆሮንቶስ 9:13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 ቅዱስ አገልግሎት የሚያከናውኑት ሰዎች ከቤተ መቅደስ የሚያገኙትን ምግብ እንደሚመገቡ እንዲሁም ዘወትር በመሠዊያው የሚያገለግሉ ከመሠዊያው የራሳቸውን ድርሻ እንደሚያገኙ አታውቁም?+
-