29 “ለእኔ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ እነሱን ለመቀደስ የምታደርገው ነገር ይህ ነው፦ እንከን የሌለበትን አንድ ወይፈንና እንከን የሌለባቸውን ሁለት አውራ በጎች ውሰድ፤+ 2 እንዲሁም ቂጣ፣ በዘይት ከተለወሰ ሊጥ የተጋገረ የቀለበት ቅርጽ ያለው እርሾ ያልገባበት ዳቦና ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ ውሰድ።+ እነዚህንም ከላመ የስንዴ ዱቄት ጋግረህ 3 በቅርጫት ውስጥ ታደርጋቸዋለህ፤ በቅርጫት ውስጥ አድርገህም+ ከወይፈኑና ከሁለቱ አውራ በጎች ጋር ታቀርባቸዋለህ።