3 ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ+ እንዲሆን የሚቃጠል መባም+ ሆነ ለየት ያለ ስእለት ለመሳል የሚቀርብ መሥዋዕት ወይም የፈቃደኝነት መባ+ አሊያም በየወቅቱ በምታከብሯቸው በዓላት+ ላይ የሚቀርብ መባ፣ ከከብታችሁ ወይም ከመንጋችሁ በመውሰድ ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ በምታቀርቡበት ጊዜ 4 መባውን የሚያቀርበው ሰው በአንድ አራተኛ ሂን ዘይት የተለወሰ አንድ አሥረኛ ኢፍ የላመ ዱቄትም+ የእህል መባ አድርጎ ለይሖዋ ማቅረብ ይኖርበታል።