ዘሌዋውያን 3:16, 17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ካህኑም እንደ ምግብ ይኸውም ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ እንዳለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሳቸዋል። ስቡ ሁሉ የይሖዋ ነው።+ 17 “‘ስብም ሆነ ደም+ ፈጽሞ አትብሉ። ይህም በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለእናንተም ሆነ ለትውልዶቻችሁ ዘላቂ ደንብ ነው።’” ዘሌዋውያን 4:8-10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 “‘ከዚያም አንጀቱን የሸፈነውን ስብና በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ ጨምሮ ለኃጢአት መባ የቀረበውን ወይፈን ስብ በሙሉ ከላዩ ላይ ያነሳል፤ 9 እንዲሁም ሁለቱን ኩላሊቶችና በላያቸው ላይ ያለውን በሽንጡ አካባቢ የሚገኝ ስብ ያነሳል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳል።+ 10 ይህም ለኅብረት መሥዋዕት+ ከሚቀርበው በሬ ላይ ከሚነሳው ጋር ተመሳሳይ ይሆናል። ካህኑም የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ እንዲጨሱ ያደርጋል። 1 ሳሙኤል 2:16, 17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ሰውየውም “በመጀመሪያ ስቡን ያቃጥሉ፤+ ከዚያ በኋላ የፈለግከውን* ውሰድ” ይለው ነበር። እሱ ግን “አይሆንም፤ አሁኑኑ ስጠኝ፤ ካልሆነ ግን ነጥቄ እወስዳለሁ!” ይለዋል። 17 ሰዎቹ የይሖዋን መባ ያቃልሉ ስለነበር የአገልጋዮቹ ኃጢአት በይሖዋ ፊት እጅግ ታላቅ ሆነ።+
16 ካህኑም እንደ ምግብ ይኸውም ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ እንዳለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሳቸዋል። ስቡ ሁሉ የይሖዋ ነው።+ 17 “‘ስብም ሆነ ደም+ ፈጽሞ አትብሉ። ይህም በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለእናንተም ሆነ ለትውልዶቻችሁ ዘላቂ ደንብ ነው።’”
8 “‘ከዚያም አንጀቱን የሸፈነውን ስብና በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ ጨምሮ ለኃጢአት መባ የቀረበውን ወይፈን ስብ በሙሉ ከላዩ ላይ ያነሳል፤ 9 እንዲሁም ሁለቱን ኩላሊቶችና በላያቸው ላይ ያለውን በሽንጡ አካባቢ የሚገኝ ስብ ያነሳል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳል።+ 10 ይህም ለኅብረት መሥዋዕት+ ከሚቀርበው በሬ ላይ ከሚነሳው ጋር ተመሳሳይ ይሆናል። ካህኑም የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ እንዲጨሱ ያደርጋል።
16 ሰውየውም “በመጀመሪያ ስቡን ያቃጥሉ፤+ ከዚያ በኋላ የፈለግከውን* ውሰድ” ይለው ነበር። እሱ ግን “አይሆንም፤ አሁኑኑ ስጠኝ፤ ካልሆነ ግን ነጥቄ እወስዳለሁ!” ይለዋል። 17 ሰዎቹ የይሖዋን መባ ያቃልሉ ስለነበር የአገልጋዮቹ ኃጢአት በይሖዋ ፊት እጅግ ታላቅ ሆነ።+