-
ዘፀአት 29:24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 ሁሉንም በአሮን እጅና በወንዶች ልጆቹ እጅ ላይ አስቀምጣቸው፤ ከዚያም በይሖዋ ፊት እንደሚወዘወዝ መባ ወዲያና ወዲህ ወዝውዛቸው።
-
-
ዘሌዋውያን 8:25-27አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
25 ከዚያም ስቡን፣ ላቱን፣ አንጀቱን የሚሸፍነውን ስብ በሙሉ፣ የጉበቱን ሞራ፣ ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ያለውን ስብ እንዲሁም ቀኝ እግሩን ወሰደ።+ 26 በይሖዋ ፊት ካለው ቂጣዎች ከተቀመጡበት ቅርጫት ውስጥም እርሾ ያልገባበት የቀለበት ቅርጽ ያለው አንድ ዳቦ፣+ ዘይት የተቀባ የቀለበት ቅርጽ ያለው አንድ ዳቦና+ አንድ ስስ ቂጣ ወሰደ። ከዚያም በስቦቹና በቀኝ እግሩ ላይ አደረጋቸው። 27 በመቀጠልም ሁሉንም በአሮን መዳፍና በወንዶች ልጆቹ መዳፍ ላይ አስቀመጣቸው፤ በይሖዋ ፊት እንደሚወዘወዝ መባም ወዲያና ወዲህ ወዘወዛቸው።
-
-
ዘሌዋውያን 9:21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 ሆኖም አሮን ፍርምባዎቹንና ቀኝ እግሩን ልክ ሙሴ ባዘዘው መሠረት እንደሚወዘወዝ መባ በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ወዘወዛቸው።+
-