8 “‘ከዚያም አንጀቱን የሸፈነውን ስብና በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ ጨምሮ ለኃጢአት መባ የቀረበውን ወይፈን ስብ በሙሉ ከላዩ ላይ ያነሳል፤ 9 እንዲሁም ሁለቱን ኩላሊቶችና በላያቸው ላይ ያለውን በሽንጡ አካባቢ የሚገኝ ስብ ያነሳል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳል።+ 10 ይህም ለኅብረት መሥዋዕት+ ከሚቀርበው በሬ ላይ ከሚነሳው ጋር ተመሳሳይ ይሆናል። ካህኑም የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ እንዲጨሱ ያደርጋል።