ዘፀአት 6:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 አሮን የነአሶን+ እህት የሆነችውን የአሚናዳብን ልጅ ኤሊሼባን አገባ። እሷም ናዳብን፣ አቢሁን፣ አልዓዛርን እና ኢታምርን ወለደችለት።+ 1 ዜና መዋዕል 24:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይሁንና ናዳብ እና አቢሁ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤+ ወንዶች ልጆችም አልነበሯቸውም፤ አልዓዛር+ እና ኢታምር ግን ካህናት ሆነው ማገልገላቸውን ቀጠሉ።