-
ዘሌዋውያን 15:8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 ፈሳሽ የሚወጣው ሰው ንጹሕ በሆነ ሰው ላይ ቢተፋ የተተፋበት ሰው ልብሶቹን ማጠብ ይኖርበታል፤ ገላውንም በውኃ መታጠብ አለበት፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።
-
-
ዘሌዋውያን 22:4-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 ከአሮን ልጆች መካከል የሥጋ ደዌ+ ያለበት ወይም ፈሳሽ የሚወጣው+ ማንኛውም ሰው ንጹሕ እስኪሆን ድረስ+ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች መብላት የለበትም፤ የሞተን ሰው* በመንካት የረከሰን ሰው+ የነካ ወይም ከሰውነቱ የዘር ፈሳሽ የሚወጣው+ 5 አሊያም ርኩስ የሆነን የሚርመሰመስ ፍጡር የነካ+ ወይም ደግሞ ሊያረክሰው በሚችል በማንኛውም ዓይነት ነገር የረከሰን ሰው የነካ+ ሰው ከእነዚህ ነገሮች አይብላ። 6 እንደነዚህ ያሉ ነገሮችን የነካ ማንኛውም ሰው* እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ገላውንም በውኃ እስካልታጠበ+ ድረስ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች መብላት አይችልም።
-