-
ዘሌዋውያን 13:25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
25 ካህኑ ቁስሉን ይመረምረዋል። በቋቁቻው ላይ ያለው ፀጉር ወደ ነጭነት ከተለወጠና ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ ከሆነ ይህ በጠባሳው ላይ የወጣ የሥጋ ደዌ ነው፤ ካህኑም ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። ይህ የሥጋ ደዌ ነው።
-
-
ዘሌዋውያን 13:30አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
30 ካህኑ ቁስሉን ይመረምረዋል።+ ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ ከሆነ እንዲሁም በዚያ ቦታ ላይ ያለው ፀጉር ቢጫ ከሆነና ከሳሳ ካህኑ ያ ሰው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል፤ ይህ በራስ ቆዳ ወይም በጢም ላይ የሚወጣ ቁስል ነው። ይህ የራስ ወይም የአገጭ የሥጋ ደዌ ነው።
-
-
ዘሌዋውያን 13:42አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
42 ሆኖም በራሱ ወይም በግንባሩ ላይ ባለው በራ ላይ ቀላ ያለ ነጭ ቁስል ቢወጣበት ይህ በራሱ ወይም በግንባሩ ላይ የወጣ ሥጋ ደዌ ነው።
-
-
ዘኁልቁ 12:12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 እባክህ፣ ግማሽ አካሉ ተበልቶ የተወለደ ጭንጋፍ መስላ እንድትቀር አታድርግ!”
-