-
ዘፀአት 30:34-36አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
34 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንተም ጥሩ መዓዛ ካላቸው ቅመሞች+ ይኸውም ከሚንጠባጠብ ሙጫ፣ ከኦኒካ፣* ከሚሸት ሙጫ እንዲሁም ከንጹሕ ነጭ ዕጣን እኩል መጠን ውሰድ። 35 ከዚያም ዕጣን አድርገህ አዘጋጀው፤+ ይህም ዕጣን በብልሃት የተቀመመ፣ ጨው የተጨመረበት፣+ ንጹሕና ቅዱስ መሆን ይኖርበታል። 36 ከእሱም የተወሰነውን ወቅጠህ በማላም ራሴን ለአንተ በምገልጥበት በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ባለው ምሥክር ፊት ታስቀምጠዋለህ። ይህም ለእናንተ እጅግ ቅዱስ መሆን ይኖርበታል።
-
-
ራእይ 8:3-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 የወርቅ ጥና* የያዘ ሌላ መልአክ መጥቶ በመሠዊያው+ አጠገብ ቆመ፤ እሱም የቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎት እየተሰማ በነበረበት ወቅት በዙፋኑ ፊት ባለው በወርቁ መሠዊያ+ ላይ እንዲያቀርበው ከፍተኛ መጠን ያለው ዕጣን+ ተሰጠው። 4 በመልአኩ እጅ ያለው የዕጣኑ ጭስ እንዲሁም የቅዱሳኑ ጸሎት+ በአምላክ ፊት ወደ ላይ ወጣ። 5 ሆኖም መልአኩ ወዲያውኑ ጥናውን ይዞ ከመሠዊያው ላይ እሳት በመውሰድ ጥናውን ሞላውና እሳቱን ወደ ምድር ወረወረው። ከዚያም ነጎድጓድ፣ ድምፅ፣ የመብረቅ ብልጭታና+ የምድር ነውጥ ተከሰተ።
-