የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘሌዋውያን 11:46, 47
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 46 “‘እንስሳትን፣ የሚበርሩ ፍጥረታትን፣ በውኃዎች ውስጥ የሚንቀሳቀስን ማንኛውም ዓይነት ሕያው ፍጡር* እንዲሁም በምድር ላይ የሚርመሰመስን ፍጡር* ሁሉ በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው፤ 47 ርኩስ የሆነውንና ንጹሕ የሆነውን እንዲሁም ለመብል የሚሆነውንና ለመብል የማይሆነውን ሕያው ፍጡር ለመለየት ሕጉ ይህ ነው።’”+

  • ዘዳግም 14:4-20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 የምትበሏቸው እንስሳት እነዚህ ናቸው፦+ በሬ፣ በግ፣ ፍየል፣ 5 ርኤም፣ የሜዳ ፍየል፣ ድኩላ፣ የዱር ፍየል፣ አጋዘን፣ የዱር በግ እና የተራራ በግ። 6 ለሁለት የተከፈለ የተሰነጠቀ ሰኮና ያለውን እንዲሁም የሚያመሰኳውን ማንኛውንም እንስሳ መብላት ትችላላችሁ። 7 ሆኖም ከሚያመሰኩት ወይም የተሰነጠቀ ሰኮና ካላቸው እንስሳት መካከል እነዚህን አትብሉ፦ ግመል፣ ጥንቸልና ሽኮኮ፤ ምክንያቱም እነዚህ እንስሳት ቢያመሰኩም ሰኮናቸው ስንጥቅ አይደለም። እነሱ ለእናንተ ርኩስ ናቸው።+ 8 አሳማም እንደዚሁ ነው፤ ምክንያቱም ሰኮናው ስንጥቅ ቢሆንም አያመሰኳም። ለእናንተ ርኩስ ነው። ሥጋቸውን መብላትም ሆነ በድናቸውን መንካት የለባችሁም።

      9 “በውኃ ውስጥ ከሚኖሩ መካከል እነዚህን መብላት ትችላላችሁ፦ ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን ሁሉ መብላት ትችላላችሁ።+ 10 ሆኖም ክንፍና ቅርፊት የሌለውን ማንኛውንም ነገር አትብሉ። ለእናንተ ርኩስ ነው።

      11 “ንጹሕ የሆነውን ወፍ ሁሉ መብላት ትችላላችሁ። 12 እነዚህን ግን አትብሉ፦ ንስር፣ ዓሣ በል ጭላት፣ ጥቁር ጥምብ አንሳ፣+ 13 ቀይ ጭልፊትም ሆነ ጥቁር ጭልፊት እንዲሁም ሁሉንም ዓይነት ሌሎች ጭልፊቶች፣ 14 ማንኛውንም ዓይነት ቁራ፣ 15 ሰጎን፣ ጉጉት፣ ዓሣ አዳኝ ወፍ፣ ማንኛውንም ዓይነት ሲላ፣ 16 ትንሿ ጉጉት፣ ባለ ረጅም ጆሮ ጉጉት፣ ዝይ፣ 17 ሻላ፣ ጥምብ አንሳ፣ ለማሚት፣ 18 ራዛ፣ ማንኛውንም ዓይነት ሽመላ፣ ጅንጅላቴና የሌሊት ወፍ። 19 በተጨማሪም ክንፍ ያላቸው የሚርመሰመሱ ፍጥረታት* በሙሉ ለእናንተ ርኩስ ናቸው። መበላት የለባቸውም። 20 ንጹሕ የሆነን ማንኛውንም የሚበር ፍጥረት መብላት ትችላላችሁ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ