-
ዘሌዋውያን 11:4-8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 “‘ሆኖም የሚያመሰኩትን ወይም ሰኮናቸው የተሰነጠቀውን እነዚህን እንስሳት መብላት የለባችሁም፦ ግመል የሚያመሰኳ ቢሆንም ሰኮናው የተሰነጠቀ አይደለም። ለእናንተ ርኩስ ነው።+ 5 ሽኮኮም+ መብላት የለባችሁም፤ ምክንያቱም የሚያመሰኳ ቢሆንም ሰኮናው የተሰነጠቀ አይደለም። ለእናንተ ርኩስ ነው። 6 ጥንቸልም ብትሆን መብላት የለባችሁም፤ ምክንያቱም የምታመሰኳ ብትሆንም ሰኮናዋ የተሰነጠቀ አይደለም። ለእናንተ ርኩስ ነች። 7 አሳማም+ መብላት የለባችሁም፤ ሰኮናው የተሰነጠቀና ስንጥቁ ሙሉ በሙሉ የተከፈለ ቢሆንም እንኳ አያመሰኳም። ለእናንተ ርኩስ ነው። 8 የእነዚህን እንስሳት ሥጋ አትብሉ ወይም በድናቸውን አትንኩ። እነዚህ ለእናንተ ርኩስ ናቸው።+
-