የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘኁልቁ 28:26-31
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 26 “‘መጀመሪያ የሚደርሰው ፍሬ በሚሰበሰብበት ቀን+ ለይሖዋ አዲስ የእህል መባ ስታቀርቡ+ በሳምንታት በዓላችሁ ላይ ቅዱስ ጉባኤ አድርጉ።+ ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም።+ 27 ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ እንዲሁም እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው የሚቃጠል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤+ 28 ከእነዚህም ጋር ለእያንዳንዱ ወይፈን ሦስት አሥረኛ መስፈሪያ፣ ለአውራው በግ ደግሞ ሁለት አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት የእህል መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ 29 እንዲሁም ለሰባቱ ተባዕት የበግ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው አንድ አሥረኛ መስፈሪያ በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት ታቀርባላችሁ፤ 30 በተጨማሪም ለእናንተ ማስተሰረያ እንዲሆን አንድ የፍየል ጠቦት ታቀርባላችሁ።+ 31 ከዘወትሩ የሚቃጠል መባና ከእህል መባው በተጨማሪ እነዚህን ታቀርባላችሁ። እንስሳቱም እንከን የሌለባቸው መሆን አለባቸው፤+ ከመጠጥ መባቸውም ጋር መቅረብ ይኖርባቸዋል።

  • ዘዳግም 16:16
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 16 “በመካከልህ ያሉ ወንዶች ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ ይኸውም በቂጣ በዓል+ ቀን፣ በሳምንታት በዓል+ ቀን እንዲሁም በዳስ* በዓል+ ቀን አምላክህ ይሖዋ በመረጠው ስፍራ ፊቱ ይቅረቡ፤ ማናቸውም ባዶ እጃቸውን ይሖዋ ፊት አይቅረቡ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ