29 “ይህም ለእናንተ ዘላቂ ደንብ ሆኖ ያገለግላል፦ በሰባተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን ራሳችሁን አጎሳቁሉ፤ ምንም ዓይነት ሥራም አትሥሩ፤+ የአገራችሁ ሰውም ሆነ በመካከላችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ምንም ዓይነት ሥራ አይሥራ። 30 በዚህ ቀን፣ ንጹሕ መሆናችሁን ለማሳወቅ ለእናንተ ማስተሰረያ+ ይቀርባል። በይሖዋም ፊት ከኃጢአታችሁ ሁሉ ንጹሕ ትሆናላችሁ።+ 31 ይህ ሙሉ በሙሉ የምታርፉበት ሰንበት ነው፤ እናንተም ራሳችሁን አጎሳቁሉ።+ ይህም ዘላቂ ደንብ ነው።