27 “‘ማንኛውም ሰው ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራ አንድ ዓመት ገደማ የሆናት አንዲት ፍየል የኃጢአት መባ አድርጎ ያቅርብ።+ 28 ከዚያም ባለማወቅ በይሖዋ ፊት ኃጢአት በመሥራት የተሳሳተው ሰው ኃጢአቱ ይሰረይለት ዘንድ ካህኑ ማስተሰረያ ያቀርብለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል።+ 29 ባለማወቅ ከሚፈጸም ነገር ጋር በተያያዘ በእስራኤላውያን መካከል ለሚገኝ የአገሬው ተወላጅም ሆነ በመካከላቸው ለሚኖር የባዕድ አገር ሰው አንድ ዓይነት ሕግ ይኑራችሁ።+