-
ዘፀአት 12:49አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
49 ለአገሩ ተወላጅም ሆነ በመካከላችሁ ለሚኖር የባዕድ አገር ሰው ሕጉ አንድ ዓይነት ነው።”+
-
-
ዘሌዋውያን 24:22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 “‘ለባዕድ አገሩም ሰው ሆነ ለአገሬው ተወላጅ፣ ለሁላችሁም የሚሠራው አንድ ዓይነት ድንጋጌ ነው፤+ ምክንያቱም እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’”
-
-
ዘኁልቁ 15:15አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 የጉባኤው ክፍል የሆናችሁት እናንተም ሆናችሁ አብሯችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው አንድ ዓይነት ደንብ ይኖራችኋል። ይህም በትውልዶቻችሁ ሁሉ ዘላቂ ደንብ ይሆናል። የባዕድ አገሩ ሰው በይሖዋ ፊት ልክ እንደ እናንተ ይታያል።+
-