-
ዘዳግም 15:7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 “ከወንድሞችህ መካከል አንዱ አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ከሚገኙት ከተሞች በአንዱ ውስጥ ድሃ ቢሆን በድሃው ወንድምህ ላይ ልብህ አይጨክንበት ወይም እጅህን አትጠፍበት።+
-
-
መዝሙር 41:1አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
41 ለተቸገረ ሰው የሚያስብ ደስተኛ ነው፤+
በመከራ ቀን ይሖዋ ይታደገዋል።
-
-
መዝሙር 112:5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 በልግስና የሚያበድር ሰው ይሳካለታል።+
י [ዮድ]
ጉዳዩን በፍትሕ ያከናውናል።
-
-
1 ጢሞቴዎስ 6:18አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 በተጨማሪም መልካም ነገር እንዲያደርጉ፣ በመልካም ሥራዎች ባለጸጋ እንዲሆኑ እንዲሁም ለጋሶችና ለሌሎች ለማካፈል ዝግጁ እንዲሆኑ ምከራቸው፤+
-
-
1 ዮሐንስ 3:17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 ይሁን እንጂ የዚህ ዓለም ቁሳዊ ንብረት ያለው ሰው ወንድሙ ሲቸገር ተመልክቶ ሳይራራለት ቢቀር ‘የአምላክ ፍቅር በእሱ ውስጥ አለ’ እንዴት ሊባል ይችላል?+
-