-
ዘሌዋውያን 11:21-24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 “‘በአራቱም እግራቸው ከሚሄዱ ክንፍ ካላቸው የሚርመሰመሱ ፍጥረታት መካከል መብላት የምትችሉት ከእግሮቻቸው በላይ በመሬት ላይ ለመፈናጠር የሚያገለግል የሚተጣጠፍ ቅልጥም ያላቸውን ብቻ ነው። 22 ከእነዚህም መካከል የሚከተሉትን መብላት ትችላላችሁ፦ የተለያየ ዓይነት የሚፈልስ አንበጣ፣ ሌሎች የሚበሉ አንበጦች፣+ እንጭራሪቶችና ፌንጣዎች። 23 አራት እግር ኖሯቸው ክንፍ ያላቸው ሌሎች የሚርመሰመሱ ፍጥረታት ሁሉ ለእናንተ አስጸያፊ ናቸው። 24 በእነዚህ ራሳችሁን ታረክሳላችሁ። በድናቸውን የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።+
-
-
ዘዳግም 14:8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 አሳማም እንደዚሁ ነው፤ ምክንያቱም ሰኮናው ስንጥቅ ቢሆንም አያመሰኳም። ለእናንተ ርኩስ ነው። ሥጋቸውን መብላትም ሆነ በድናቸውን መንካት የለባችሁም።
-