-
ዘፍጥረት 14:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 የሚጨቁኑህን በእጅህ አሳልፎ የሰጠህ፣
ልዑሉ አምላክ ይወደስ!”
አብራምም ከሁሉም ነገር ላይ አንድ አሥረኛውን ሰጠው።+
-
-
ዘፍጥረት 28:22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 እንደ ዓምድ ያቆምኩት ይህ ድንጋይም የአምላክ ቤት ይሆናል፤+ አምላክ ሆይ፣ እኔም ከምትሰጠኝ ከማንኛውም ነገር አንድ አሥረኛውን ለአንተ እሰጣለሁ።”
-
-
ዘኁልቁ 18:21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 “እንግዲህ የሌዊ ወንዶች ልጆች ለሚያከናውኑት አገልግሎት ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ ለሚሰጡት አገልግሎት በእስራኤል ውስጥ ያለውን የማንኛውንም ነገር አንድ አሥረኛ ውርሻ አድርጌ እንደሰጠኋቸው+ ልብ በል።
-