ዘሌዋውያን 1:4, 5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ለሚቃጠል መባ በሚቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ይጫን፤ መባውም ለሰውየው ማስተሰረያ ይሆን ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል። 5 “‘ከዚያም ወይፈኑ በይሖዋ ፊት ይታረድ፤ ካህናት+ የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን ያቅርቡት፤ እንዲሁም ደሙን በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በሚገኘው መሠዊያ ጎኖች ሁሉ ላይ ይርጩት።+ ዘሌዋውያን 7:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ለበደል መባ የሚሆነውን እንስሳ፣ ለሚቃጠል መባ የሚሆነውን እንስሳ በሚያርዱበት ቦታ ያርዱታል፤ ደሙም+ በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ መረጨት ይኖርበታል።+ ዕብራውያን 9:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 አዎ፣ በሕጉ መሠረት ሁሉም ነገር ማለት ይቻላል በደም ይነጻል፤+ ደም ካልፈሰሰ በስተቀር ይቅርታ ማግኘት አይቻልም።+
4 ለሚቃጠል መባ በሚቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ይጫን፤ መባውም ለሰውየው ማስተሰረያ ይሆን ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል። 5 “‘ከዚያም ወይፈኑ በይሖዋ ፊት ይታረድ፤ ካህናት+ የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን ያቅርቡት፤ እንዲሁም ደሙን በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ በሚገኘው መሠዊያ ጎኖች ሁሉ ላይ ይርጩት።+