-
ዘሌዋውያን 6:14-16አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 “‘የእህል መባ ሕግ ደግሞ ይህ ነው፦+ እናንተ የአሮን ወንዶች ልጆች በመሠዊያው ፊት ለፊት በይሖዋ ፊት ታቀርቡታላችሁ። 15 ከመካከላቸው አንዱ ለእህል መባ ከቀረበው የላመ ዱቄት ላይ ከነዘይቱ አንድ እፍኝ ያነሳል፤ እንዲሁም በእህል መባው ላይ ያለውን ነጭ ዕጣን በሙሉ ይወስዳል። አምላክ መላውን መባ እንዲያስበውም ለይሖዋ ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል።+ 16 ከዚያ የተረፈውን አሮንና ወንዶች ልጆቹ ይበሉታል፤+ እንደ ቂጣ ተጋግሮ በቅዱስ ስፍራ ይበላል። በመገናኛ ድንኳኑ ግቢ ውስጥ ይበሉታል።+
-
-
1 ቆሮንቶስ 9:13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 ቅዱስ አገልግሎት የሚያከናውኑት ሰዎች ከቤተ መቅደስ የሚያገኙትን ምግብ እንደሚመገቡ እንዲሁም ዘወትር በመሠዊያው የሚያገለግሉ ከመሠዊያው የራሳቸውን ድርሻ እንደሚያገኙ አታውቁም?+
-