ዘሌዋውያን 10:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 በኋላም የአሮን ወንዶች ልጆች ናዳብና አቢሁ+ እያንዳንዳቸው የዕጣን ማጨሻቸውን አምጥተው በላዩ ላይ እሳት አደረጉበት፤ በእሳቱም ላይ ዕጣን ጨመሩበት።+ ከዚያም ይሖዋ እንዲያደርጉ ያላዘዛቸውን ያልተፈቀደ እሳት+ በፊቱ አቀረቡ። 2 በዚህ ጊዜ እሳት ከይሖዋ ፊት ወጥቶ በላቸው፤+ እነሱም በይሖዋ ፊት ሞቱ።+ ዘኁልቁ 3:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 የአሮን ወንዶች ልጆች ስም ይህ ነው፦ የበኩር ልጁ ናዳብ፣ አቢሁ፣+ አልዓዛርና+ ኢታምር።+ ዘኁልቁ 3:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ይሁንና ናዳብና አቢሁ በሲና ምድረ በዳ በይሖዋ ፊት ያልተፈቀደ እሳት ባቀረቡ ጊዜ በይሖዋ ፊት ሞቱ፤+ እነሱም ወንዶች ልጆች አልነበሯቸውም። አልዓዛርና+ ኢታምር+ ግን ከአባታቸው ከአሮን ጋር በክህነት ማገልገላቸውን ቀጠሉ። 1 ዜና መዋዕል 24:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይሁንና ናዳብ እና አቢሁ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤+ ወንዶች ልጆችም አልነበሯቸውም፤ አልዓዛር+ እና ኢታምር ግን ካህናት ሆነው ማገልገላቸውን ቀጠሉ።
10 በኋላም የአሮን ወንዶች ልጆች ናዳብና አቢሁ+ እያንዳንዳቸው የዕጣን ማጨሻቸውን አምጥተው በላዩ ላይ እሳት አደረጉበት፤ በእሳቱም ላይ ዕጣን ጨመሩበት።+ ከዚያም ይሖዋ እንዲያደርጉ ያላዘዛቸውን ያልተፈቀደ እሳት+ በፊቱ አቀረቡ። 2 በዚህ ጊዜ እሳት ከይሖዋ ፊት ወጥቶ በላቸው፤+ እነሱም በይሖዋ ፊት ሞቱ።+
4 ይሁንና ናዳብና አቢሁ በሲና ምድረ በዳ በይሖዋ ፊት ያልተፈቀደ እሳት ባቀረቡ ጊዜ በይሖዋ ፊት ሞቱ፤+ እነሱም ወንዶች ልጆች አልነበሯቸውም። አልዓዛርና+ ኢታምር+ ግን ከአባታቸው ከአሮን ጋር በክህነት ማገልገላቸውን ቀጠሉ።