-
ዘዳግም 1:26-28አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
26 እናንተ ግን ወደዚያ ለመውጣት ፈቃደኞች አልሆናችሁም፤ በአምላካችሁ በይሖዋ ትእዛዝም ላይ ዓመፃችሁ።+ 27 በየድንኳኖቻችሁ ውስጥ ሆናችሁ እንዲህ በማለት አጉተመተማችሁ፦ ‘ይሖዋ ስለጠላን አሞራውያን እንዲያጠፉን ለእነሱ አሳልፎ ሊሰጠን ከግብፅ ምድር አወጣን። 28 ታዲያ የምንሄደው ወዴት ነው? ወንድሞቻችን “ሰዎቹ ከእኛ ይልቅ ብርቱና ረጃጅሞች ናቸው፤ ከተሞቻቸውም ቢሆኑ ታላላቅና እስከ ሰማይ በሚደርስ ቅጥር የታጠሩ ናቸው፤+ እንዲያውም በዚያ የኤናቅን+ ልጆች አይተናል” በማለት ልባችን እንዲቀልጥ አድርገዋል።’+
-