የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፀአት 23:31-33
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 31 “ወሰንህንም ከቀይ ባሕር አንስቶ እስከ ፍልስጤማውያን ባሕር እንዲሁም ከምድረ በዳው አንስቶ እስከ ወንዙ* ድረስ አደርገዋለሁ።+ ምክንያቱም የምድሩን ነዋሪዎች በእጃችሁ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ አንተም ከፊትህ አባረህ ታስወጣቸዋለህ።+ 32 ከእነሱም ሆነ ከአማልክታቸው ጋር ቃል ኪዳን መግባት የለብህም።+ 33 በእኔ ላይ ኃጢአት እንድትሠራ እንዳያደርጉህ በምድርህ ላይ መኖር የለባቸውም። አማልክታቸውን ብታገለግል ወጥመድ ይሆንብሃል።”+

  • ዘዳግም 7:3, 4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 ከእነሱ ጋር በጋብቻ አትዛመድ። ሴቶች ልጆችህን ለወንዶች ልጆቻቸው አትዳር ወይም ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንዶች ልጆችህ አትውሰድ።+ 4 ምክንያቱም ልጆችህ ሌሎች አማልክትን ያገለግሉ ዘንድ እኔን ከመከተል ዞር እንዲሉ ያደርጓቸዋል፤+ ከዚያም የይሖዋ ቁጣ በእናንተ ላይ ይነድዳል፤ አንተንም ወዲያው ያጠፋሃል።+

  • ኢያሱ 23:12, 13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 “ይሁንና ወደ ኋላ ዞር ብትሉና ከእነዚህ ብሔራት መካከል ተርፈው ከእናንተ ጋር ከቀሩት+ ሰዎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት ብትመሠርቱ፣ በጋብቻ ብትዛመዱ+ እንዲሁም እናንተ ከእነሱ ጋር ብትወዳጁ፣ እነሱም ከእናንተ ጋር ወዳጅነት ቢመሠርቱ 13 አምላካችሁ ይሖዋ ከዚህ በኋላ ለእናንተ ሲል እነዚህን ብሔራት እንደማያባርራቸው* በእርግጥ እወቁ።+ እነሱም አምላካችሁ ይሖዋ ከሰጣችሁ ከዚህች መልካም ምድር ላይ እስክትጠፉ ድረስ ወጥመድ፣ አሽክላ፣ ለጀርባችሁ ጅራፍ እንዲሁም በዓይናችሁ ውስጥ እንዳለ እሾህ ይሆኑባችኋል።+

  • መሳፍንት 2:2, 3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 2 እናንተም ከዚህች ምድር ነዋሪዎች ጋር ቃል ኪዳን አትግቡ፤+ መሠዊያዎቻቸውንም አፈራርሱ።’+ እናንተ ግን ቃሌን አልሰማችሁም።+ እንዲህ ያደረጋችሁት ለምንድን ነው? 3 በዚህም የተነሳ ‘እነሱን ከፊታችሁ አላስወጣቸውም፤+ ለእናንተም ወጥመድ ይሆኑባችኋል፤+ አማልክታቸውም ያታልሏችኋል’+ አልኩ።”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ