ዘኁልቁ 3:30, 31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 የቀአታውያን ቤተሰቦች የአባቶች ቤት አለቃ የዑዚኤል+ ልጅ ኤሊጻፋን ነበር። 31 ኃላፊነታቸውም ከታቦቱ፣+ ከጠረጴዛው፣+ ከመቅረዙ፣+ ከመሠዊያዎቹ፣+ በቅዱሱ ስፍራ ለማገልገል ከሚጠቀሙባቸው ዕቃዎች፣+ ከመከለያውና*+ ከእነዚህ ጋር ግንኙነት ካለው አገልግሎት ሁሉ ጋር የተያያዘ ነበር።+ ዘኁልቁ 4:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 “አሮንና ወንዶች ልጆቹ ሰፈሩ ከመነሳቱ በፊት በቅዱሱ ስፍራ ያሉትን ነገሮችና የቅዱሱን ስፍራ ዕቃዎች በሙሉ ሸፍነው መጨረስ አለባቸው።+ ከዚያም የቀአት ወንዶች ልጆች ለመሸከም ይመጣሉ፤+ ሆኖም በቅዱሱ ስፍራ ያሉትን ነገሮች መንካት የለባቸውም፤ ከነኩ ግን ይሞታሉ።+ ከመገናኛ ድንኳኑ ጋር በተያያዘ እነዚህን ነገሮች የማከናወኑ ኃላፊነት* የተጣለው በቀአት ወንዶች ልጆች ላይ ነው።
30 የቀአታውያን ቤተሰቦች የአባቶች ቤት አለቃ የዑዚኤል+ ልጅ ኤሊጻፋን ነበር። 31 ኃላፊነታቸውም ከታቦቱ፣+ ከጠረጴዛው፣+ ከመቅረዙ፣+ ከመሠዊያዎቹ፣+ በቅዱሱ ስፍራ ለማገልገል ከሚጠቀሙባቸው ዕቃዎች፣+ ከመከለያውና*+ ከእነዚህ ጋር ግንኙነት ካለው አገልግሎት ሁሉ ጋር የተያያዘ ነበር።+
15 “አሮንና ወንዶች ልጆቹ ሰፈሩ ከመነሳቱ በፊት በቅዱሱ ስፍራ ያሉትን ነገሮችና የቅዱሱን ስፍራ ዕቃዎች በሙሉ ሸፍነው መጨረስ አለባቸው።+ ከዚያም የቀአት ወንዶች ልጆች ለመሸከም ይመጣሉ፤+ ሆኖም በቅዱሱ ስፍራ ያሉትን ነገሮች መንካት የለባቸውም፤ ከነኩ ግን ይሞታሉ።+ ከመገናኛ ድንኳኑ ጋር በተያያዘ እነዚህን ነገሮች የማከናወኑ ኃላፊነት* የተጣለው በቀአት ወንዶች ልጆች ላይ ነው።