ዘፍጥረት 29:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 ዳግመኛም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እሷም “ይሖዋ እንዳልተወደድኩ ስለሰማ ይሄኛውንም ልጅ ሰጠኝ” አለች። ስሙንም ስምዖን*+ አለችው። ዘፍጥረት 46:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 የስምዖን+ ወንዶች ልጆች የሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ጾሃር እንዲሁም ከአንዲት ከነአናዊት የወለደው ሻኡል ነበሩ።+ ዘኁልቁ 2:12, 13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ከእሱ ቀጥሎ የሚሰፍረው የስምዖን ነገድ ይሆናል፤ የስምዖን ልጆች አለቃ የጹሪሻዳይ ልጅ ሸሉሚኤል+ ነው። 13 በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 59,300 ናቸው።+
12 ከእሱ ቀጥሎ የሚሰፍረው የስምዖን ነገድ ይሆናል፤ የስምዖን ልጆች አለቃ የጹሪሻዳይ ልጅ ሸሉሚኤል+ ነው። 13 በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 59,300 ናቸው።+