የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘኁልቁ 4:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 “አሮንና ወንዶች ልጆቹ ሰፈሩ ከመነሳቱ በፊት በቅዱሱ ስፍራ ያሉትን ነገሮችና የቅዱሱን ስፍራ ዕቃዎች በሙሉ ሸፍነው መጨረስ አለባቸው።+ ከዚያም የቀአት ወንዶች ልጆች ለመሸከም ይመጣሉ፤+ ሆኖም በቅዱሱ ስፍራ ያሉትን ነገሮች መንካት የለባቸውም፤ ከነኩ ግን ይሞታሉ።+ ከመገናኛ ድንኳኑ ጋር በተያያዘ እነዚህን ነገሮች የማከናወኑ ኃላፊነት* የተጣለው በቀአት ወንዶች ልጆች ላይ ነው።

  • ዘኁልቁ 4:24-26
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 24 የጌድሶናውያን ቤተሰቦች እንዲንከባከቡና እንዲሸከሙ+ የተመደቡት እነዚህን ነገሮች ነው፦ 25 እነሱም የማደሪያ ድንኳኑን የድንኳን ጨርቆች፣+ የመገናኛ ድንኳኑን ጨርቆች፣ መደረቢያውንና ከእሱ በላይ ያለውን ከአቆስጣ ቆዳ የተሠራ መደረቢያ+ እንዲሁም የመገናኛ ድንኳኑን መግቢያ መከለያ*+ ይሸከማሉ፤ 26 በተጨማሪም የግቢውን መጋረጃዎች፣+ በማደሪያ ድንኳኑና በመሠዊያው ዙሪያ ባለው ግቢ መግቢያ ላይ የሚገኘውን መከለያ፣*+ የድንኳን ገመዶቻቸውንና ዕቃዎቻቸውን በሙሉ እንዲሁም ለአገልግሎቱ የሚውሉትን ነገሮች ሁሉ ይሸከማሉ። የሥራ ምድባቸው ይህ ነው።

  • ዘኁልቁ 4:31-33
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 31 በመገናኛ ድንኳኑ ከሚያከናውኑት አገልግሎት ጋር በተያያዘ የሚከተሉትን ነገሮች የመሸከም ኃላፊነት+ ተጥሎባቸዋል፦ የማደሪያ ድንኳኑን ቋሚዎች፣+ አግዳሚ እንጨቶቹን፣+ ዓምዶቹን፣+ መሰኪያዎቹን፣+ 32 በግቢው ዙሪያ ያሉትን ቋሚዎች፣+ መሰኪያዎቻቸውን፣+ የድንኳን ካስማዎቻቸውን፣+ የድንኳን ገመዶቻቸውን እንዲሁም ቁሳቁሶቻቸውንና ከዚህ አገልግሎት ጋር የተያያዙትን ነገሮች ሁሉ ይሸከማሉ። በኃላፊነት የሚሸከሙትንም ዕቃ በስም ጠቅሰህ ትመድብላቸዋለህ። 33 የሜራሪ ወንዶች ልጆች ቤተሰቦች+ በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር አመራር ሥር ሆነው በመገናኛ ድንኳኑ የሚያገለግሉት በዚህ መሠረት ነው።”+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ