-
ዘኁልቁ 13:26አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
26 በቃዴስ+ ባለው በፋራን ምድረ በዳ ወደሚገኙት ወደ ሙሴ፣ ወደ አሮንና ወደ መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ተመልሰው መጡ። ያዩትንም ሁሉ ለመላው ማኅበረሰብ ተናገሩ፤ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።
-
-
ዘዳግም 1:1, 2አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
1 ሙሴ በዮርዳኖስ ክልል በሚገኘው ምድረ በዳ ይኸውም በፋራን፣ በጦፌል፣ በላባ፣ በሃጼሮት እና በዲዛሃብ መካከል ከሚገኘው ከሱፈ ፊት ለፊት ባለው በረሃማ ሜዳ ላይ ለነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ የተናገረው ቃል ይህ ነው። 2 ወደ ሴይር ተራራ በሚወስደው መንገድ በኩል ከኮሬብ እስከ ቃዴስበርኔ+ የ11 ቀን መንገድ ነው።
-