ዘፍጥረት 49:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ሴሎ* እስኪመጣ ድረስ በትረ መንግሥት ከይሁዳ፣+ የአዛዥም በትር ከእግሮቹ መካከል አይወጣም፤+ ለእሱም ሕዝቦች ይታዘዙለታል።+ መዝሙር 2:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 በብረት በትረ መንግሥት ትሰብራቸዋለህ፤+እንደ ሸክላ ዕቃም ታደቃቸዋለህ።”+ መዝሙር 72:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ነገሥታትም ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ፤ብሔራትም ሁሉ ያገለግሉታል። ራእይ 6:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 እኔም አየሁ፣ እነሆ ነጭ ፈረስ ነበር፤+ በእሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፤ አክሊልም ተሰጠው፤+ እሱም ድል እያደረገ ወጣ፤ ድሉንም ለማጠናቀቅ ወደ ፊት ገሰገሰ።+ ራእይ 19:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 እሱም ብሔራትን ይመታበት ዘንድ ከአፉ ረጅም ስለታም ሰይፍ+ ይወጣል፤ እንደ እረኛም በብረት በትር ይገዛቸዋል።*+ በተጨማሪም ሁሉን ቻይ የሆነውን የአምላክን የመዓቱን የቁጣ ወይን ጠጅ መጭመቂያ ይረግጣል።+
2 እኔም አየሁ፣ እነሆ ነጭ ፈረስ ነበር፤+ በእሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፤ አክሊልም ተሰጠው፤+ እሱም ድል እያደረገ ወጣ፤ ድሉንም ለማጠናቀቅ ወደ ፊት ገሰገሰ።+
15 እሱም ብሔራትን ይመታበት ዘንድ ከአፉ ረጅም ስለታም ሰይፍ+ ይወጣል፤ እንደ እረኛም በብረት በትር ይገዛቸዋል።*+ በተጨማሪም ሁሉን ቻይ የሆነውን የአምላክን የመዓቱን የቁጣ ወይን ጠጅ መጭመቂያ ይረግጣል።+