-
ዘፀአት 22:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 “ለይሖዋ ካልሆነ በቀር ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው ይገደል።+
-
-
ዘፀአት 32:25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
25 በተቃዋሚዎቻቸው ፊት መሳለቂያ እንዲሆኑ አሮን ሕዝቡን መረን ስለለቀቃቸው ሙሴ ሕዝቡ መረን እንደተለቀቀ አስተዋለ።
-
-
ዘፀአት 32:27አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
27 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እያንዳንዳችሁ ሰይፋችሁን ታጠቁ፤ ከአንዱ በር ወደ ሌላው በር በመሄድና በሰፈሩ ውስጥ በማለፍ እያንዳንዱ ሰው ወንድሙን፣ ጎረቤቱንና የቅርብ ጓደኛውን ይግደል።’”+
-
-
ዘዳግም 13:6-9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 “የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ አሊያም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ጓደኛህ* ‘ሌሎች አማልክትን እናምልክ’+ በማለት በሚስጥር ሊያባብልህ ቢሞክርና እነዚህ አማልክት ደግሞ አንተም ሆንክ አባቶችህ የማታውቋቸው 7 እንዲሁም በቅርብም ሆነ በሩቅ፣ ከአንዱ የምድር ጫፍ እስከ ሌላኛው የምድር ጫፍ የሚገኙ በዙሪያህ ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኳቸው አማልክት ቢሆኑ 8 እሺ አትበለው ወይም አትስማው+ አሊያም አትዘንለት ወይም ደግሞ አትራራለት፤ ከለላም አትሁነው፤ 9 ከዚህ ይልቅ ያለማመንታት ግደለው።+ እሱን ለመግደል መጀመሪያ እጅህን መሰንዘር ያለብህ አንተ ነህ፤ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እጁን ይሰንዝርበት።+
-